ወደ ኸሚስ ሙሸይት የተተኮሱ ሁለት ባለስቲክ ሚሳኤሎች ተጠልፈው እንዲወድሙ ተደርጓል። ይህን ያስታወቁት በየመን ሕጋዊነትን ለመደገፍ የተቋቋመው ጥምረት ኃይሎች ይፋዊ ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ቱርኪ አል-ማልኪ ናቸው።

አል-ማልኪ እንዳሉት ሚሳኤሎቹን የተኮሰው “አሸባሪው የሁቲ ሚሊሻ” ሲሆን፣ ጥቃቱ ከተማዋን ዒላማ ያደረገ የሽብር ጥቃት ነው።