ወደ ሪያድ የተተኮሰ አንድ ባለስቲክ ሚሳኤል ተጠልፎ እንዲወድም ተደርጓል። ይህን ያስታወቁት በየመን ሕጋዊነትን ለመደገፍ የተቋቋመው ጥምረት ኃይሎች ይፋዊ ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ቱርኪ አል-ማልኪ ናቸው።

አል-ማልኪ እንዳሉት ሚሳኤሉን የተኮሰው “አሸባሪው የሁቲ ሚሊሻ” ሲሆን፣ ጥቃቱ የሳዑዲ አረቢያን ዋና ከተማ ዒላማ ያደረገ የሽብር ጥቃት ነው።