ሳዑዲ ጋዜት እንደዘገበው፣ የሳዑዲ አረቢያ የማዘጋጃ ቤቶችና የቤቶች ሚኒስቴር ፀጉር አስተካካዮች የሚያገለግል የጤና ሰርተፊኬት እንዲኖራቸው፣ የግል ንጽሕናቸውን እንዲጠብቁና አገልግሎት ከመስጠታቸው በፊትና በሚሰጡበት ወቅት ትክክለኛ የጤና አሠራሮችን እንዲከተሉ ግዴታ ጥሏል። ፈቃድ ካለው ተቋም ውጭ በደንበኞች ቤት የፀጉር አገልግሎት ለመስጠት ልዩ ፈቃድ እንደሚያስፈልግም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የወንዶች ፀጉር ቤቶች ደጋግመው የሚጠቀሙባቸውን መሣሪያዎች ከእያንዳንዱ አገልግሎት በኋላ ማጽዳት፣ ከጀርም ነጻ ማድረግና ማምከን አለባቸው፤ አንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን ደግሞ ወዲያውኑ ማስወገድ ይጠበቅባቸዋል። ሁሉንም መሣሪያዎቻቸውንም በየጊዜው ማጽዳትና ማምከን ይኖርባቸዋል።