ሳዑዲ ጋዜት የሲቪል መከላከያን በኤክስ ላይ የወጣ መግለጫ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ማክሰኞ በመካ ድንገተኛ ጎርፍ ሦስት ሕጻናትን ወስዷል። ጥሪ የደረሳቸው የነፍስ አድን ቡድኖች አንዱን ሕጻን ማትረፍ ሲችሉ ሌላው ሕጻን ሕይወቱ አልፎ ተገኝቷል።

እንደ ሲቪል መከላከያ ገለጻ፣ የሦስተኛውን የጠፋ ሕጻን ፍለጋ አሁንም ቀጥሏል።

ተቋሙ ዜጎች፣ ነዋሪዎችና ጎብኚዎች በዝናብ ወቅት ከሸለቆዎችና ውሃ ከሚጠራቀምባቸው ቦታዎች እንዲርቁ አሳስቧል።