የሳዑዲ ብሔራዊ የሜትሮሎጂ ማዕከል ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጪው ረቡዕ ድረስ በመካ ክልል በሚገኙ በርካታ አስተዳደሮች መካከለኛ እስከ ከባድ ዝናብ እንደሚጥል ተንብዩአል።
ትንበያው ቅድስት የመካ ከተማን እንዲሁም አል-ካሚል፣ አል-ጁሙም፣ ባህራ፣ ጣኢፍ፣ መይሳን፣ አድሀም፣ አል-አርዲያት፣ አል-ሊስ እና አል-ቁንፉዛን ያካትታል።
የሲቪል መከላከያ ዋና ዳይሬክቶሬት ሁሉም ሰው ጥንቃቄ እንዲያደርግና በዝናቡ ወቅት ለደህንነቱ ሲባል ያወጣቸውን መመሪያዎችና ምክሮች እንዲከተል ጥሪ አቅርቧል።
