የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፈይሰል ቢን ፋርሐን ቢን አብዱላህ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን አሸባሪው የሁቲ ቡድን በመንግሥቱ ሲቪል አካባቢዎች ላይ የሚያደርሰውን ቀጣይ ጥቃት አውግዘዋል።
ውግዘቱ የተገለጸው የኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለልዑል ፈይሰል ባደረጉት የስልክ ጥሪ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች በቀጣናው ያሉ የቅርብ ጊዜ ሁኔታዎችንም ገምግመዋል።
ሚኒስትሮቹ የጋራ የገልፍ እንቅስቃሴን ለመደገፍ፣ ውጥረትን ለማርገብና እንዳይስፋፋ ለመከላከል እንዲሁም የቀጣናውን ደኅንነትና መረጋጋት ለመጠበቅ ጥረቶችን መቀጠልና ቅንጅትንና ምክክርን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።
