የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፈይሰል ቢን ፋርሐን ቢን አብዱላህ እና የቱርክ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን አሸባሪው የሁቲ ቡድን በመንግሥቱ ላይ የሚያደርሰውን ቀጣይ ጥቃት አውግዘዋል።

ሚኒስትሮቹ ውግዘታቸውን የገለጹት የቱርኩ ሚኒስትር ለልዑል ፈይሰል ባደረጉት የስልክ ጥሪ ሲሆን በቀጣናው ያለው ሁኔታ የሚገኝበትንም ደረጃ ተወያይተዋል።

በተጨማሪም የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን፣ ሁለቱ ወንድማማች አገሮች ወቅታዊ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም የሚያደርጉትን ጥረት እና የቀጣናውን ደኅንነትና መረጋጋት ለማጠናከር የጀመሩትን የጋራ እንቅስቃሴ ገምግመዋል።