የሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ልዑል ፈይሰል ቢን ፈርሃን ቢን አብዱላህ ከኩዌት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ ጀራህ ጃቤር አል-አሕመድ አል-ሳባሕ የስልክ ጥሪ ተቀብለዋል። በውይይቱ ሁለቱ ሚኒስትሮች አሸባሪው የሁቲ ቡድን በሳዑዲ ዓረቢያ ሲቪል አካባቢዎች ላይ የሚፈጽመውን ቀጣይ ጥቃት አውግዘዋል።
የሳዑዲ የዜና ወኪል (SPA) እንደዘገበው፣ ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መካከል ያለውን የቅርብ ወንድማማችነት ግንኙነት ገምግመዋል፤ በቀጣናው ስላሉ ወቅታዊ ሁኔታዎችም ተወያይተዋል።
ሚኒስትሮቹ የሁለቱን ወንድማማች ሀገራት ደኅንነትና መረጋጋት የሚጎዳ ማንኛውንም ነገር በመጋፈጥ ሳዑዲ ዓረቢያ እና ኩዌት በአጋርነት እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።
