በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ የተካሄደው የእስላማዊ ትብብር ድርጅት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤት 52ኛ ጉባኤ አሸባሪው የሁቲ ቡድን በሳዑዲ ዓረቢያ ላይ የፈጸማቸውን ጥቃቶች አውግዟል፤ ከእነዚህም መካከል መካ፣ መዲና፣ አውሮፕላን ማረፊያዎች፣ መሠረተ ልማቶችና ሲቪል ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ይገኙበታል።
በጉባኤው ላይ የሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ልዑል ፈይሰል ቢን ፈርሃን ቢን አብዱላህን ወክለው በድርጅቱ የሳዑዲ ዓረቢያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ኻሊድ ቢን ሙሐመድ አል-ሸሪፍ ተሳትፈዋል።
ጉባኤው በቀጣናው ወቅታዊ ሁኔታዎች፣ እስላማዊውን ዓለም በሚመለከቱ ጉዳዮች እና የጋራ ሥራን ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይቷል።
በተጨማሪም ደኅንነትን፣ መረጋጋትን፣ እድገትንና ብልጽግናን ለማረጋገጥ በማለም የእስላማዊ ሀገራትን ደኅንነትና የሕዝቦቻቸውን ጥቅም የሚመለከቱ በርካታ ጉዳዮች ተነስተዋል።


