አል ሪያድ ጋዜጣ እንደዘገበው፣ የአደጋ ጊዜ ብሔራዊ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መድረክ በሪያድ የማስጠንቀቂያ ደወል አሰምቶ ዜጎችና ነዋሪዎች ይፋዊ መመሪያዎችን እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል።

መድረኩ ሰዎች በሕንፃዎች ውስጥ ወደሚገኝ ቅርብ ደኅንነቱ የተጠበቀ ቦታ እንዲሄዱና ከመስኮቶች፣ ከክፍት ቦታዎችና ከአደገኛ ስፍራዎች እንዲርቁ ጠይቋል። አደጋው እስኪያልፍ ድረስ ማንም እንዳይወጣ፣ መሰባሰብና ፎቶ ወይም ቪዲዮ ማንሳትም እንዲቀር አሳስቧል።

በተጨማሪም የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት በይፋዊ መንገዶች የሚያወጧቸውን መመሪያዎች እንዲከተሉ አሳስቧል።