አውስትራሊያ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥትን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን አውግዛለች። ጥቃቶቹንም «ተቀባይነት የሌላቸው» ስትል የገለጸች ሲሆን በተለይም በዋና ከተማዋ ሪያድ በሚገኘው የንጉሥ ኻሊድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ጠቅሳለች።
የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ ሀገራቸው በመንግሥቱ ላይ የተፈጸሙትን ጥቃቶች እንደምታወግዝ ገልጸዋል። በሪያድ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የደረሰው ጥቃት በርካታ ንጹሐን ሰዎችን ለሞትና ለጉዳት መዳረጉንም ጠቁመዋል።
ሚኒስትሯ በሳዑዲ አረቢያ ሲቪሎችንና የሲቪል መሠረተ ልማቶችን ዒላማ የሚያደርጉ ጥቃቶች በአስቸኳይ መቆም እንዳለባቸው አሳስበዋል።
