የፍልስጤም ፕሬዚዳንታዊ ጽሕፈት ቤት አሸባሪው የሁቲ ቡድን በሳዑዲ ዓረቢያ ላይ እየፈጸማቸው ያሉትን ጥቃቶች አውግዟል፤ ጥቃቶቹንም ወሳኝ ተቋማትን፣ አውሮፕላን ማረፊያዎችንና መሠረተ ልማቶችን ያነጣጠሩ የሽብር ጥቃቶች ብሏቸዋል።

ጽሕፈት ቤቱ የሳዑዲ ዓረቢያንና የሁለቱን ቅዱሳን መስጊዶች ደኅንነት መንካት በመላው የእስልምና ዓለም ቅዱሳት ስፍራዎች ላይ የሚፈጸም ጥቃት መሆኑን አሳስቧል።

በተለይም በዋና ከተማዋ ሪያድ በሚገኘው የንጉሥ ኻሊድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የተፈጸሙትን ጥቃቶች ያወገዘ ሲሆን፣ የፍልስጤም መንግሥት በእነዚህ የሽብር ጥቃቶች ፊት ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር ሙሉ በሙሉ የመቆም ጽኑ አቋሙን በድጋሚ አረጋግጧል።

ጽሕፈት ቤቱ ሳዑዲ ዓረቢያ ደኅንነቷን፣ መረጋጋቷንና ተቋሞቿን ለመጠበቅ ለምትወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ ፍጹም ድጋፉን ገልጿል።