የንጉሥ ሰልማን የሰብአዊ እርዳታና የድጋፍ ማዕከል (KSrelief) በየመን ሪፐብሊክ ኤደን ግዛት አል-ቡረይቃ ወረዳ በሚገኙት አል-ሻዕብ «2» እና አል-ሮውዳ መጠለያ ጣቢያዎች 40 የመጠለያ ቁሳቁሶችን አከፋፍሏል። ከእርዳታው የ40 ተፈናቃይ ቤተሰቦች 185 አባላት ተጠቃሚ ሆነዋል።
ቤተሰቦቹ በቅርቡ በተከሰቱ ሁኔታዎች ምክንያት ከሁደይዳ ግዛት ሃይስ እና አል-ኸውኻ ወረዳዎች እንዲሁም ከታዒዝ ግዛት አል-ሞኻ እና መውዘዕ ወረዳዎች ተፈናቅለው ወደ ኤደን የመጡ ናቸው።
ስርጭቱ በየመን የአስቸኳይ ጊዜ የመጠለያ ዕቅድ አምስተኛ ምዕራፍ አካል ነው። ሳዑዲ አረቢያ በሰብአዊ ክንፏ በንጉሥ ሰልማን የእርዳታ ማዕከል አማካይነት በዓለም ዙሪያ የተፈናቀሉና ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ስቃይ ለማቃለል ከምታከናውናቸው የእርዳታና የሰብአዊ ፕሮጀክቶች አንዱም ነው።
