የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያና በዩክሬን መካከል በሚካሄደው ጦርነት የኢነርጂ ዘርፍን ብቻ የሚመለከት የተኩስ አቁም ዛሬ ተግባራዊ መሆኑን አስታውቀዋል።
ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተባለው የማኅበራዊ ሚዲያ መድረካቸው ባሰፈሩት መልእክት ሁለቱም ወገኖች በኢነርጂ ዘርፍ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን ገልጸው፣ ስምምነቱን መጣስ እንደማይገባም አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዚዳንቱ በመልእክታቸው «ከዚህ ሰዓት ጀምሮ በሩሲያና በዩክሬን ጦርነት በኢነርጂ ዘርፍ የተኩስ አቁም ተግባራዊ ሆኗል» ብለዋል። ስምምነቱ እንዴት እንደሚተገበር ወይም ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ግን ተጨማሪ ዝርዝር አልሰጡም።
