ዩናይትድ ኪንግደም አሸባሪው የሁቲ ሚሊሻ በአብሃ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያና በንጉሥ ኻሊድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ልማቶች ላይ የፈጸመውን የሽብር ጥቃት አጥብቃ አውግዛለች። ጥቃቶቹ በበርካታ ዜጎችና በአገሪቱ በሚኖሩ ነዋሪዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት አድርሰዋል።

የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ፣ የኮመንዌልዝና የልማት ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፣ ሚሊሻው የሚፈጽማቸውን ግድየለሽ ሲል የገለጻቸውን ጥቃቶች በመመከት ረገድ ዩናይትድ ኪንግደም ከሳዑዲ ዓረቢያ ጎን እንደምትቆም አስታውቋል።

ሁለቱ አውሮፕላን ማረፊያዎች መንገደኞች የሚጠቀሙባቸው የሲቪል ተቋማት ሲሆኑ እነሱን ዒላማ ማድረግ የዜጎችንና የነዋሪዎችን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል የሽብር ወንጀል ነው።