በየመን ሕጋዊ መንግሥትን የሚደግፈው ጥምር ኃይል፣ አሸባሪው የሁቲ ሚሊሻ ወደ ሳዑዲ ከተሞች የተኮሳቸው ሶስቱም ባሊስቲክ ሚሳኤሎች ተጠልፈው መውደማቸውን ገልጿል።

የጥምር ኃይሉ ኦፊሴላዊ ቃል አቀባይ ሜጀር ጀነራል ቱርኪ አል-ማሊኪ እንደተናገሩት፣ ከሚሳኤሎቹ ሁለቱ ወደ ዋና ከተማዋ ሪያድ የተተኮሱ ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ ወደ ኸሚስ ሙሸይጥ ተተኩሷል። ቃል አቀባዩ ሶስቱም ሚሳኤሎች ተጠልፈው መውደማቸውን አረጋግጠዋል።

ይህ የሚሳኤል ተኩስ ሚሊሻው በሳዑዲ ከተሞችና በነዋሪዎቻቸው ደኅንነት ላይ ያነጣጠረ የሽብር ጥቃት ነው።