የሳዑዲ አረቢያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የጉብኝት ቪዛ የያዙ ሰዎችን ወደ መካ ከተማና ወደ ቅዱሳት ስፍራዎች ለማድረስ የሚያጓጉዝ ወይም ለማጓጓዝ የሚሞክር ማንኛውም ሰው እስከ 100,000 ሪያል የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት አሳስቧል። ውሳኔው ከዙል ቂዕዳ ወር የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እስከ ዙል ሒጃ ወር 14ኛው ቀን መጨረሻ ድረስ ተግባራዊ ይሆናል።

ሚኒስቴሩ እንዳለው፣ ለዚህ ጥሰት ጥቅም ላይ መዋሉ የተረጋገጠ የየብስ ተሽከርካሪ የአጓጓዡ፣ የተባባሪው ወይም ከእርሱ ጋር የተመሳጠረው ሰው ንብረት ከሆነ የሚመለከተው ፍርድ ቤት እንዲወርሰው ይጠየቃል።

ሚኒስቴሩ ሁሉም ሰው የሐጅ ሕጎችንና መመሪያዎችን እንዲያከብር ጥሪ አቅርቧል። እነዚህ ሕጎች ሐጃጆች ሥርዓተ አምልኳቸውን በቀላሉና በእርጋታ እንዲፈጽሙ ደኅንነታቸውንና ጸጥታቸውን ለመጠበቅ ያለሙ መሆናቸውን ገልጿል።

ሕጉን የሚጥሱ ሰዎችን በመካ፣ በመዲና፣ በሪያድና በምሥራቃዊ ክልል በ911፣ በተቀሩት የመንግሥቱ ክልሎች ደግሞ በ999 ስልክ ቁጥር ማሳወቅ እንደሚቻል ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

በሳዑዲ አረቢያ ለሚኖሩ አሽከርካሪዎች፣ በትራንስፖርት ሥራ ለተሰማሩና ለኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለውጭ አገር ነዋሪዎች ቤተሰቦች ይህ ማሳሰቢያ ጠቃሚ ነው፤ በሐጅ ወቅት ሕጉን መጣስ ከባድ የገንዘብ ቅጣትና የተሽከርካሪ መወረስ ሊያስከትል ይችላል።