የሳዑዲ አረቢያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ማንኛውንም ዓይነት የጉብኝት ቪዛ የጠየቀ ሰው፣ ቪዛው የተሰጠው ግለሰብ ያለ ፈቃድ ሐጅ ካደረገ ወይም ለማድረግ ከሞከረ፣ አሊያም ወደ መካ ከተማና ቅዱሳት ስፍራዎች ከገባ ወይም እዚያ ከቆየ፣ እስከ 100,000 ሪያል የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ቅጣቱ ቪዛ ተሰጥቷቸው ጥሰቱን በፈጸሙ ሰዎች ቁጥር ልክ እንደሚደጋገም ገልጿል፤ ይህም ማለት ለእያንዳንዱ ጥሰት የፈጸመ ሰው የተለየ ቅጣት ይጣላል። ስለዚህ ለሌሎች የጉብኝት ቪዛ የሚጠይቁ ሰዎች ይህን ደንብ በጥንቃቄ ማወቅና ማጤን ይኖርባቸዋል።
ሚኒስቴሩ ሁሉም ሰው የ1447 ሂጅራ የሐጅ ወቅት መመሪያዎችን እንዲያከብርና ለሐጃጆች ደኅንነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል፤ መመሪያዎቹን የሚጥሱ ሕጋዊ ቅጣት እንደሚጠብቃቸውም አረጋግጧል።
ጥሰቶችን በመካ፣ በመዲና፣ በሪያድና በምሥራቃዊ ክልል 911፣ በሌሎች የመንግሥቱ ክልሎች ደግሞ 999 በመደወል ማሳወቅ ይቻላል።
ይህ ማስጠንቀቂያ ለዘመዶቻቸው ወይም ለሚያውቋቸው ሰዎች የጉብኝት ቪዛ ለሚጠይቁ በሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በቀጥታ የሚመለከት ነው።
