የሳዑዲ አረቢያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የድንበር ደኅንነት ሕግን የጣሱ ሰዎች ወደ መንግሥቱ እንዲገቡ የሚያመቻች፣ በአገር ውስጥ የሚያጓጉዛቸው፣ መጠለያ የሚሰጣቸው ወይም በማንኛውም መንገድ እርዳታና አገልግሎት የሚያቀርብላቸው ሰው እስከ 15 ዓመት እስራትና እስከ 1 ሚሊዮን ሪያል የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቀው አስታውቋል።
በተጨማሪም ለማጓጓዣ የዋለው ተሽከርካሪና ለመጠለያ ያገለገለው መኖሪያ ሊወረስ፣ የጥፋተኛው ማንነትም ለሕዝብ ይፋ ሊደረግ ይችላል።
ሚኒስቴሩ እንዳለው ድርጊቱ እስር የሚያስከትል ከባድ ወንጀል ሲሆን ክብርንና ታማኝነትን የሚያጎድፍ ወንጀል ተደርጎ ይወሰዳል።
ሚኒስቴሩ ሁሉም ሰው የመኖሪያ፣ የሥራና የድንበር ደኅንነት ደንቦችን እንዲያከብር ጠይቋል። ጥሰቶችን በመካ፣ በመዲና፣ በሪያድና በምሥራቃዊ ክልል በ911፣ በሌሎች የመንግሥቱ ክልሎች ደግሞ በ999 ማሳወቅ ይቻላል።
