በየመን ሕጋዊነትን ለመመለስ የተቋቋመው ጥምረት ይፋዊ ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል ቱርኪ አል-ማሊኪ እንዳስታወቁት፣ የጥምረቱ ኃይሎች በሳዑዲ አረቢያ ምሥራቃዊ ግዛት እና በሪያድ ክልል ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትተው አውድመዋል።

የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ያሰራጨው መግለጫ ድሮኖቹን ማን እንዳስወነጨፋቸው ወይም መቼ እንደተመቱ አልጠቀሰም፤ ስለደረሰ ጉዳትም ምንም አላለም።