በየመን ሕጋዊነትን ለመመለስ የተቋቋመው ጥምረት ኃይሎች አሸባሪው የሁቲ ቡድን ወደ ኸሚስ ሙሻይት ከተማ ያስወነጨፋቸውን ሁለት ባለስቲክ ሚሳኤሎች መትተው በማውደም የቡድኑን ሌላ የሽብር ጥቃት አክሽፈዋል።

የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ እንደዘገበው፣ የጥምረቱ ይፋዊ ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል ቱርኪ አል-ማሊኪ ሁለቱን ሚሳኤሎች ያስወነጨፈው “አሸባሪው የሁቲ ሚሊሻ” መሆኑን ገልጸዋል። መግለጫው ስለደረሰ ጉዳት ወይም ጉዳተኞች ምንም አልጠቀሰም።