ኬንያ አሸባሪው የሁቲ ቡድን በሳዑዲ ዓረቢያ ላይ የፈጸመውን ጥቃት አውግዛለች። የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ ለሳዑዲ ዓረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባደረጉት የስልክ ጥሪ ይህንን አቋም አሳውቀዋል።

ሙዳቫዲ በውይይቱ “አሸባሪው የሁቲ ሚሊሻ” ሲሉ የጠሩት ቡድን በመንግሥቱ፣ በሲቪል ተቋማቱና በወሳኝ መሠረተ ልማቶቹ ላይ ያደረሰውን ጥቃት አውግዘዋል። ኬንያ በእነዚህ የሽብር ዛቻዎች ፊት ከሳዑዲ ዓረቢያ ጎን እንደምትቆምም ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ በጥቃቶቹ ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች ቤተሰቦች እንዲሁም ለሳዑዲ መንግሥትና ሕዝብ የኬንያን ጥልቅ ሐዘን አስተላልፈው ለቆሰሉት ፈጣን ማገገምን ተመኝተዋል።