በሳዑዲ ዓረቢያ የመዲና ክልል አንድ ክሩዝ ሚሳኤል ተጠልፎ መውደሙን በየመን ህጋዊ መንግሥትን የሚደግፈው ጥምረት አስታውቋል።

ማስታወቂያውን የሰጡት የጥምረቱ ኃይሎች ኦፊሴላዊ ቃል አቀባይ ሜጀር ጀነራል ቱርኪ አል-ማሊኪ ሲሆኑ፣ ስለ ክስተቱ ሌላ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።