ኦካዝ ጋዜጣ እንደዘገበው፣ የሳዑዲ ፓስፖርት ጠቅላይ ዳይሬክቶሬት (ጀዋዛት) በሳዑዲ ዓረቢያ ያለ ሕጋዊ ፈቃድ የሚኖሩ የመን ዜጎች ሁኔታቸውን እንዲያስተካክሉ በመንግሥቱ ሁሉም ክልሎች የተሰራጩ 21 ቦታዎችን ወስኗል።
በሪያድ ቦታዎቹ የሁለተኛው ኢንዱስትሪያል ከተማ ፓስፖርት ቢሮ፣ በአል-ሃኢር አስተዳደራዊ ማዕከል የሚገኘው የፓስፖርት አስተዳደር፣ የአል-ማላዝ ፓስፖርት ቅርንጫፍና የአል-ኻርጅ ግዛት ፓስፖርት ቢሮ ናቸው። በምሥራቃዊ ክልል ደግሞ በአል-ኹባር፣ በአል-አሕሳና በደቡብ ሐፍር አል-ባጢን ፓስፖርት ቢሮዎች ይስተናገዳል።
በዐሲር ክልል የክልሉ ፓስፖርት አስተዳደርና የኸሚስ ሙሸይጥና የቢሻ ቢሮዎች ሲወሰኑ፣ በመካ ክልል በአል-ሹመይሲ የሕዝብ አገልግሎት ማዕከል የማስተካከያ ቢሮ ተቋቁሟል፤ ሌሎች ቦታዎችም አሉ።
