በሳዑዲ ዓረቢያ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ልዑል አብዱልአዚዝ ቢን ሳዑድ መመሪያ መሠረት የሕዝብ ደህንነት ዳይሬክተር በተለያዩ ሙያዎች የሚያገለግሉ 2440 አባላትን ወደሚቀጥለው ማዕረግ ያሳደጉ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል።

ዳይሬክተሩ ለደህንነት አባላት ለሚሰጠው ትኩረት የአገሪቱን አመራር ያመሰገኑ ሲሆን በሁሉም ዘርፎች ላደረጉት ድጋፍም የአገር ውስጥ ሚኒስትሩን አመስግነዋል።

ማዕረግ ያደጉትን አባላት እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ዳይሬክተሩ በሥራቸው ስኬት እንዲገጥማቸው ተመኝተው፣ ዕድገቱ ሃይማኖታቸውን፣ ንጉሣቸውንና አገራቸውን በበለጠ ትጋት እንዲያገለግሉ ማነሳሳት እንዲሆን ተስፋቸውን ገልጸዋል።