ማሌዢያ በሳዑዲ አረቢያ ሲቪሎችን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን አውግዛለች። የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ ሐሰን ይህን አቋም የገለጹት ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፈይሰል ቢን ፋርሃን ቢን አብዱላህ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ነው።
የማሌዢያው ሚኒስትር በውይይቱ መጀመሪያ ላይ ሀገራቸው ጥቃቶቹን እንደምታወግዝ ገልጸው ከመንግሥቱ ጎን መቆሟን አረጋግጠዋል። ሳዑዲ አረቢያ ሉዓላዊነቷን፣ ደህንነቷንና መረጋጋቷን ለማስጠበቅ እንዲሁም ዜጎቿንና በግዛቷ የሚኖሩ ነዋሪዎችን ለመጠበቅ የምትወስዳቸውን እርምጃዎች ሁሉ ማሌዢያ እንደምትደግፍም ተናግረዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች የሁለትዮሽ ግንኙነቱን የገመገሙ ሲሆን በቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች እንዲሁም የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል።
