የሳዑዲው አል-ናስር በእስያ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ኤሊት ሻምፒዮንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ በሪያድ በሚገኘው የንጉሥ ሳዑድ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የኡዝቤኪስታኑን ነፍጭ ፈርጋና 3 ለ 1 አሸንፏል።

በ33ኛው ደቂቃ አንጄሎ ለአል-ናስር የመጀመሪያውን ግብ ያስቆጠረ ሲሆን በ42ኛው ደቂቃ ፖርቱጋላዊው ኮከብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ሁለተኛውን ግብ አክሎ ቡድኑ የመጀመሪያውን አጋማሽ 2 ለ 0 እየመራ አጠናቋል።

በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ በ51ኛው ደቂቃ ኦዲሎቭ ለእንግዳው ቡድን አንድ ግብ ቢመልስም፣ በኋላ ጎፉሮቭ በራሱ መረብ ላይ ያስቆጠራት ግብ አል-ናስር ጨዋታውን 3 ለ 1 እንዲያጠናቅቅ አድርጋለች።

በዚህ ድል አል-ናስር በመጀመሪያው ዙር በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶቹ አል-ዓይን 4 ለ 0 ከተሸነፈ በኋላ በሊጉ ምዕራፍ የመጀመሪያ ሦስት ነጥቦቹን አግኝቷል። ነፍጭ የኢራቁን አል-ቁዋ አል-ጀዊያ 1 ለ 0 በማሸነፍ ባገኛቸው ሦስት ነጥቦች ቀርቷል።