የሳዑዲው አል-ኢቲሃድ ዛሬ በጂዳ የንጉሥ አብዱላህ ስፖርት ከተማ ስታዲየም ባስተናገደው የ2026-2027 የኤኤፍሲ ቻምፒየንስ ሊግ ኢሊት የምዕራብ ዞን ሁለተኛ ዙር ጨዋታ እንግዳው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ክለብ ሸባብ አል-አህሊ 2 ለ 1 አሸንፎታል።

የሸባብ አል-አህሊን ሁለቱንም ግቦች ሰርዳር አዝሙን በ7ኛውና በ16ኛው ደቂቃ ያስቆጠረ ሲሆን፣ የአል-ኢቲሃድን ብቸኛ ግብ ሪቻርድ ሪዮስ በ66ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።

በዚህ ውጤት ሸባብ አል-አህሊ ነጥቡን 6 ሲያደርስ፣ አል-ኢቲሃድ በአንድ ነጥብ ቀርቷል።