የእስራኤል ወራሪ ኃይሎች እሑድ ምሽት በደቡባዊ ሶሪያ የቁነይጥራ ግዛት ገጠራማ አካባቢ ወደምትገኘው ሐሚዲያ ከተማና ወደ መዝረዓት አል-ሐኑት ዘልቀው በመግባት ቤቶችን በኃይል ገብተው የፈተሹ ሲሆን በመኖሪያ ሰፈሮችም ውስጥ ተሰማርተዋል።

የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት፣ 4 ተሽከርካሪዎችን ያካተተ የወራሪ ኃይል ቡድን በማዕከላዊ ቁነይጥራ ገጠር በምትገኘው ሐሚዲያ መንደር ቤቶችን ወሯል። ሌላ ወታደራዊ ቡድን ደግሞ በደቡባዊው ገጠር ወደሚገኘው የመዝረዓት አል-ሐኑት ምዕራባዊ ሰፈር ገብቶ በቤቶቹ መካከል ከተሰማራ በኋላ ወደ ሰማይ ተኩሶ ለቅቋል። በዚሁ ጊዜ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በአካባቢው ሰማይ ላይ ሲያንዣብቡ ነበር።

ከዚህ ቀደም እሑድ ጠዋት አንድ የወራሪ ኃይል ቡድን በዳራ ገጠር ወደሚገኘው የያርሙክ ተፋሰስ አካባቢና ወደ ጀምላና ዓቢዲን ከተሞች የገባ ሲሆን፣ ሌላ ቡድን ደግሞ በቁነይጥራ ገጠር ወደምትገኘው ሳይዳ አል-ሐኑት መንደር ገስግሷል።

ወራሪ ኃይሎቹ በደቡባዊ ሶሪያ በተደጋጋሚ በሚያካሂዷቸው ሰርጎ መግባቶችና ወረራዎች የ1974ቱን የኃይል ማላቀቅ ስምምነት መጣሳቸውን ቀጥለዋል። ሶሪያ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህን ለማስቆም እርምጃ እንዲወስድና ወራሪው ከግዛቷ ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ እንዲያስገድድ ጥሪዋን አድሳለች።