አሻርቅ አል-አውሳጥ ጋዜጣ እንደዘገበው፣ የሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ልዑል ፈይሰል ቢን ፈርሓን ቢን አብዱላህ ከሶሪያ አቻቸው አስዓድ አል-ሸይባኒ ጋር በቀጣናው የቅርብ ጊዜ ክስተቶች ላይ ተወያይተዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች የቀጣናውን ደኅንነትና መረጋጋት ለመደገፍ ሪያድና ደማስቆ በጋራ የሚያደርጉትን ጥረትም ገምግመዋል።