ዘ አስትሮፊዚካል ጆርናል ሌተርስ በተሰኘው መጽሔት ላይ የወጣ ጥናት እንዳመለከተው፣ 500 ሜትር ዲያሜትር ያለው የቻይናው FAST የሬዲዮ ቴሌስኮፕ ብርቅዬ በሆነ የሦስት ኮከቦች ሥርዓት ውስጥ ፑልሳር ለይቶ አግኝቷል። ሥርዓቱ ነጭ ድንክ ኮከብንና አሁንም በዕድገት ሂደት ላይ ያለ ፀሐይ መሰል ኮከብን ያካትታል።

ተመራማሪዎቹ እንደገለጹት ሥርዓቱ በጽንፈኛ ሁኔታዎች ውስጥ የኮከቦችን ዕድገትና የስበት መስተጋብሮችን ለማጥናት እንዲሁም መሠረታዊ የስበት ንድፈ ሐሳቦችን ለመፈተሽ ዕድል ይሰጣል። ፑልሳር የያዘ ሁለተኛው የሚታወቅ የሦስት ኮከቦች ሥርዓት መሆኑንም አመልክተዋል።

በሌላ ዜና ቻይና ከሃይናን ግዛት ሎንግ ማርች-12 ሮኬትን ያመጠቀች ሲሆን፣ ሮኬቱ በዝቅተኛ ምህዋር የሚሠሩ የኢንተርኔት ሳተላይቶችን 27ኛ ቡድን አስቀድሞ በተወሰነው ምህዋር ላይ በስኬት አስቀምጧል።