የሳዑዲ አረቢያ አገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የሐጅ ደንቦችንና መመሪያዎችን በመጣስ ያለ ፈቃድ ዜጎችን ወይም ነዋሪዎችን ሲያጓጉዝ የተያዘ ማንኛውም ሰው እስከ 50,000 ሪያል የገንዘብ ቅጣትና እስከ 6 ወር የሚደርስ እስራት እንደሚጣልበት አረጋግጧል።
በተጨማሪም ለማጓጓዝ ያገለገለው የየብስ ተሽከርካሪ በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲወረስ ጥያቄ ይቀርባል። አጓጓዡ የውጭ ዜጋ ከሆነ ቅጣቱን ከጨረሰ በኋላ ከአገር የሚባረር ሲሆን በሕግ ለተወሰነው ጊዜ ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንዳይገባ ይከለከላል።
ሚኒስቴሩ ሕጋዊ የሐጅ ፈቃድ ማግኘት ሐጅን ለመፈጸም መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን አሳስቧል። ሁሉም ሰው የዘንድሮውን (1447 ሂጅራ) የሐጅ ወቅት መመሪያዎች እንዲያከብርና ለሐጃጆች ደህንነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንዲተባበር ጥሪ ያቀረበ ሲሆን መመሪያዎቹን የሚጥሱ ሕጋዊ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ገልጿል።
ሚኒስቴሩ ጥሰቶችን በመካ፣ በመዲና፣ በሪያድና በምሥራቃዊ ክልል በ911፣ በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ደግሞ በ999 እንዲጠቁሙ ጥሪ አቅርቧል። በሳዑዲ አረቢያ በሾፌርነት ወይም በተሽከርካሪ ባለቤትነት ለሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ይህ ማስጠንቀቂያ በተለይ ትኩረት የሚሻ ነው።
