የሳዑዲ ቀይ ጨረቃ ባለሥልጣን የመዲና ቅርንጫፍ የአምቡላንስ ቡድኖች በነቢዩ መስጊድ የጁምዓ ሶላት ላይ ሳሉ ድንገተኛ የጤና ችግር ያጋጠማቸውን የ84 ዓመት ሕንዳዊት የዑምራ ተጓዥ የልብ ምት መመለስ ችለዋል። የሳዑዲ ዜና አገልግሎት (SPA) እንደዘገበው ይህ የተከናወነው ሰጋጆችንና ጎብኚዎችን ለማገልገል በተዘጋጀው የአምቡላንስ ስምሪት ዕቅድ መሠረት ነው።

ቡድኑ በ56 ሰከንድ ደርሶ አስፈላጊውን የድንገተኛ ሕክምና የሰጠ ሲሆን፣ የልብ ምታቸው እስኪመለስ ድረስ የልብና የሳንባ ማነቃቂያ (CPR) አድርጓል። ከዚያም ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ባብ ጂብሪል ጤና ጣቢያ ተወስደዋል።

የመዲና ቅርንጫፍ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሕመድ ቢን ዓሊ አዝ-ዘህራኒ ፈጣኑ ምላሽ ቡድኖቹ በነቢዩ መስጊድና በአካባቢው ባላቸው ከፍተኛ ዝግጁነትና በታቀደ የመስክ ስምሪት የተገኘ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም በወሳኝ ጊዜያት እንክብካቤ ለመስጠትና ሕይወትን የማዳን ዕድልን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

ዶ/ር አዝ-ዘህራኒ የቡድኖቹን ብቃትና ፈጣን ምላሽ አድንቀው፣ ባለሥልጣኑ ሰጋጆችን፣ የዑምራ ተጓዦችንና የመዲና ጎብኚዎችን ለማገልገል ዝግጁነቱን ማሳደጉን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።