የሳዑዲ ዓረቢያ ንጉሣዊ ፍርድ ቤት (ሮያል ኮርት) ዛሬ ባወጣው መግለጫ ልዑል አብዱልአዚዝ ቢን ሳዑድ ቢን ናስር ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ማረፋቸውን አስታውቋል። ዜናውን የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግቧል።

በመግለጫው መሠረት የልዑሉ የጀናዛ ሶላት ኢንሻአላህ ነገ ቅዳሜ፣ 1/4/1448 ሂጅራ፣ ከዐስር ሶላት በኋላ በሪያድ ከተማ በሚገኘው የኢማም ቱርኪ ቢን አብዱላህ ታላቅ መስጊድ ይሰገዳል።

ንጉሣዊው ፍርድ ቤት አላህ ለሟቹ ሰፊ እዝነቱን፣ ምህረቱንና ውዴታውን እንዲቸራቸውና ሰፊ ጀነትን እንዲያወርሳቸው ዱዓ አድርጓል። መግለጫው «እኛ የአላህ ነን፤ ወደ እርሱም ተመላሾች ነን» በሚለው ቃል ተጠናቋል።