በየመን ሕጋዊነትን ለመመለስ የተቋቋመው ጥምረት ኃይሎች ወደ ሳዑዲ አረቢያ ምስራቅ ክልል አቅጣጫ የተተኮሰ አንድ ድሮንን መትተው አውድመዋል። መረጃውን የሰጡት የጥምረቱ ኦፊሴላዊ ቃል አቀባይ ሜጀር ጀነራል ቱርኪ አል-ማሊኪ ናቸው።

ቃል አቀባዩ ድሮኑን ማን እንደተኮሰው አልገለጹም፤ መግለጫው ስለደረሰ ጉዳትም ምንም አልጠቀሰም።