ሳውዲ ጋዜት እንደዘገበው፣ በሰው ሀብትና ማኅበራዊ ልማት ሚኒስቴር ሥር የሚገኘው የቂዋ መድረክ ተቋማትን በሚቀጥሯቸው ሠራተኞች ብዛት በሰባት ምድቦች የሚከፍል የምደባ ሥርዓት አብራርቷል።

አነስተኛ ተቋማት በሁለት ምድቦች፣ መካከለኛ ተቋማት በሦስት ምድቦች ሲከፈሉ፣ ትልልቅና እጅግ ትልልቅ ተቋማት እያንዳንዳቸው አንድ ምድብ አላቸው።

'አነስተኛ (ሀ)' ምድብ አምስት ወይም ከዚያ በታች ሠራተኞች ያሏቸውን ተቋማት ሲያካትት፣ 'አነስተኛ (ለ)' ምድብ ደግሞ ከዚያ በላይ ሠራተኞች ያሏቸውን ይሸፍናል።