የሳዑዲ ዓረቢያ ብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ማዕከል ዛሬ በጂዛን ክልል ከመካከለኛ እስከ ከባድ ዝናብ እንደሚጥል አስጠንቅቋል። ዝናቡ በጣም ኃይለኛ ነፋስ፣ ወደ ዜሮ የተጠጋ የአግድም እይታ፣ በረዶ፣ ጎርፍና ነጎድጓድ ይታከልበታል።

ማስጠንቀቂያው የጂዛን ከተማንና የአል-ሐርስ፣ የአድ-ዳይር (በኒ ማሊክ)፣ የአር-ሪስ፣ የአል-ዓሪዳ፣ የአል-ዒዳቢ፣ የፊፋ፣ የሐሩብ፣ የአጥ-ጡዋል፣ የሳምጣ፣ የአሐድ አል-መሳሪሐ፣ የአቡ ዓሪሽ፣ የደመድ፣ የሰብያ፣ የአድ-ደርብና የበይሽ አውራጃዎችን እንዲሁም የአል-ፉጠይሓ ማዕከልንና የፈራሳን ደሴትን ይመለከታል።

ማዕከሉ እንዳስታወቀው ሁኔታው እስከ ምሽቱ 10 ሰዓት ድረስ ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።