ሳዑዲ ጋዜት እንደዘገበው፣ የሳዑዲ ዓረቢያ የባቡር መስመሮች (SAR) ቅዳሜ ዕለት ባወጣው መግለጫ እሁድ ኦክቶበር 11 ንጋት ላይ ከቃሲም በመጅመዓ በኩል ወደ ሪያድ የሚሄዱ ሁለት ተጨማሪ ባቡሮችን እንደሚያሰማራ አስታውቋል።

ባቡር ቁጥር 149 ከቃሲም ከሌሊቱ 12:30 ተነስቶ 1:32 ላይ መጅመዓ ይደርሳል፣ 1:40 ላይ ተነስቶ 2:58 ላይ ሪያድ ይገባል። ባቡር ቁጥር 139 ደግሞ 1:30 ላይ ከቃሲም ተነስቶ 2:32 መጅመዓ ይደርሳል፣ 2:40 ተነስቶ 3:58 ላይ ሪያድ ይደርሳል።

ኩባንያው በእነዚህ ተጨማሪ ጉዞዎች መጓዝ የሚፈልጉ ተሳፋሪዎች ትኬታቸውን በይፋዊ መንገዶቹ እንዲቆርጡ መክሯል።