አልጋ ወራሽና ጠቅላይ ሚኒስትር ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ዛሬ ከዮርዳኖስ ሐሽማዊ መንግሥት ንጉሥ ዳግማዊ አብደላ ቢን አል-ሑሴን የስልክ ጥሪ ተቀብለዋል።

በውይይቱ መጀመሪያ የዮርዳኖሱ ንጉሥ አሸባሪው የሁቲ ቡድን በሳዑዲ ዓረቢያ ላይ እየፈጸመ ያለውን የሽብር ጥቃት አገራቸው እንደምታወግዝ ገልጸዋል።

ንጉሥ ዳግማዊ አብደላ ዮርዳኖስ የሳዑዲ ዓረቢያን ደኅንነትና የዜጎቿንና የነዋሪዎቿን ደኅንነት በሚያሰጋ ማንኛውም ነገር ፊት ሙሉ በሙሉ ከመንግሥቱ ጎን እንደምትቆምና ሀብቷን ለመጠበቅ የምትወስዳቸውን እርምጃዎች በሙሉ እንደምትደግፍ አረጋግጠዋል።