ኢንዲፔንደንት ኡርዱ እንደዘገበው፣ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሸሪፍ እሁድ ዕለት አሸባሪው የሁቲ ሚሊሻ በሪያድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በፈጸመው ጥቃት ስድስት የፓኪስታን ዜጎች መቁሰላቸውን በመስማታቸው ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ገልጸዋል። የፓኪስታን ኤምባሲ ግንኙነት ላይ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው የየመን ጥምረት ማንነቱ ያልታወቀ ተወንጫፊ በአውሮፕላን ማረፊያው አንድ ተርሚናል ላይ ወድቆ የእሳት አደጋ መከሰቱን ገልጿል። የጥምረቱ ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ቱርኪ አል-ማሊኪ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት ተወንጫፊው በንጉሥ ኻሊድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል 4 ላይ ወድቋል።
የአየር መከላከያ ሥርዓቱ በአውሮፕላን ማረፊያው አቅራቢያ አንድ ክሩዝ ሚሳኤል አክሽፎ ማውደሙንም አክለዋል።
