በደቡባዊ የአሜሪካ ክፍል በተከሰተ አውሎ ነፋስ ቢያንስ አራት ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ600 ሺህ በላይ ቤቶችና ተቋማት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸዋል።
የአሜሪካ ብሔራዊ የአውሎ ነፋስ ማዕከል እንዳስታወቀው አውሎ ነፋሱ በፍሎሪዳ ግዛት የብስ ከደረሰ በኋላ ትናንት ጥንካሬው ቀንሶ ከሃሪኬን ወደ ሞቃታማ ወይም ድኅረ-ሞቃታማ አውሎ ነፋስ ተቀይሯል፤ ከባድ ዝናብና ኃይለኛ ነፋስም አስከትሏል።
ፍሎሪዳና አላባማን ጨምሮ በሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤ ዳርቻ የሚገኙ በርካታ ግዛቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጁ ሲሆን በኃይለኛ ነፋስ፣ በከፍተኛ ማዕበልና በከባድ ዝናብ ስጋት ውስጥ ያሉ አካባቢዎች እንዲለቀቁ አዘዋል።
ከአውሎ ነፋሱ ጋር የነበረው የነፋስ ፍጥነት በሰዓት 165 ኪሎ ሜትር ደርሷል። ተፅዕኖው የኃይል ዘርፉንም የነካ ሲሆን በሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤ 63% ገደማ የነዳጅ ዘይት ምርትና 57% የጋዝ ምርት ተቋርጧል።
