በኢንዶኔዥያ ምዕራብ ጃቫ ግዛት በምትገኘው ሱካቡሚ ከተማ ዛሬ በሬክተር መለኪያ 5.7 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
የኢንዶኔዥያ የሜትሮሎጂ፣ የአየር ንብረትና የጂኦፊዚክስ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው፣ የመንቀጥቀጡ ማዕከል ከሱካቡሚ በስተደቡብ ምዕራብ 193 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በ10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ነበር። እስካሁን በሰው ሕይወትም ሆነ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የሚያመለክት ሪፖርት የለም።
ኢንዶኔዥያ «የእሳት ቀለበት» ተብሎ በሚታወቀው የፓሲፊክ ቀበቶ ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ በርካታ የቴክቶኒክ ሰሌዳዎች የሚገናኙበት በመሆኑ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የእሳተ ገሞራና የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴዎች በተደጋጋሚ ይከሰታሉ።
