የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ እንደዘገበው፣ አልጋ ወራሹና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ በጅዳ ከኦማን ሱልጣን ሀይሠም ቢን ጣሪቅ ጋር ተገናኝተዋል።

በውይይቱ በሁለቱ ወንድማማች አገሮች መካከል ያለው ግንኙነት፣ የሁለትዮሽ ትብብር ዘርፎችና ትብብሩን በተለያዩ መስኮች ለማስፋፋትና ለማሳደግ ያሉ ተስፋ ሰጪ ዕድሎች ተገምግመዋል። ሁለቱ መሪዎች በቀጣናው ወቅታዊ ሁኔታና ደህንነቱንና መረጋጋቱን ለመጠበቅ በሚደረጉ ጥረቶች ላይም መክረዋል።

ከሳዑዲ በኩል የኢነርጂ ሚኒስትርና የኢንዱስትሪና ማዕድን ሀብት ሚኒስትር ልዑል አብዱልአዚዝ ቢን ሰልማን፣ የመካ ክልል ምክትል አሚር ልዑል ሰዑድ ቢን ሚሽዓል፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፈይሰል ቢን ፈርሐን፣ የንግድ ሚኒስትር ዶክተር ማጂድ አል-ቀሰቢ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር አሕመድ አል-ኸጢብ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ሚኒስትር ሳሊሕ አል-ጃሲር፣ የኢንቨስትመንት ሚኒስትር ፈሀድ አል ሰይፍ፣ የጠቅላላ የስለላ ድርጅት ኃላፊ ኻሊድ አል-ሑመይዳንና በኦማን የሳዑዲ አምባሳደር ኢብራሂም ቢን ሰዕድ ቢን ቢሻን ተገኝተዋል።

ከኦማን በኩል የመከላከያ ጉዳዮች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሰይድ ሺሃብ ቢን ጣሪቅ አል ሰዒድ፣ የሱልጣኑ ቤተ መንግሥት ጉዳዮች ሚኒስትር ሰይድ ኻሊድ ቢን ሂላል አል-ቡሰዒዲ፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሰይድ ሐሙድ ቢን ፈይሰል አል-ቡሰዒዲ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰይድ በድር ቢን ሐመድ አል-ቡሰዒዲ፣ የኦማን ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን ኃላፊ አብዱሰላም ቢን መሐመድ አል-ሙርሺዲ፣ የኢነርጂና ማዕድን ሚኒስትር ሳሊም ቢን ናሲር አል-ዐውፊን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና በሳዑዲ ዓረቢያ የኦማን አምባሳደር ነጂብ ቢን ሂላል አል-ቡሰዒዲ ተገኝተዋል።