ባለፉት ጥቂት ሰዓታት በሳዑዲ አረቢያ የሪያድ፣ የምሥራቅና የደቡብ ክልሎች 4 ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ተጠልፈው መውደማቸውን ቅንጅቱ አስታውቋል።

ይህንን ያስታወቁት “በየመን ሕጋዊነትን የሚደግፈው ቅንጅት” ኃይሎች ይፋዊ ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ቱርኪ አል-ማልኪ ናቸው።