የሳዑዲ ዓረቢያ ብሔራዊ የሚቲዮሮሎጂ ማዕከል በምሥራቅ ግዛት ከባድ ጭጋግ እንደሚከሰት ማስጠንቀቂያ አውጥቷል። ጭጋጉ የደማምና የዳህራን ከተሞችን እንዲሁም የኑዓይሪያ፣ የኻፍጂ፣ የጁበይል፣ የራስ ታኑራ፣ የቀጢፍ፣ የኹባር፣ የዑደይድና የአል-አሕሳ አውራጃዎችን እና በሥራቸው የሚገኙ መንደሮችንና ማዕከላትን ያካልላል።
ማዕከሉ እንዳለው፣ ጭጋጉ በፍጥነት መንገዶችና ገላጣ ቦታዎች ላይ የአግድም እይታ ርቀትን ወደ 1 ኪሎ ሜትር እና ከዚያ በታች ሊቀንስ ይችላል፤ ሁኔታው በሳዑዲ ሰዓት አቆጣጠር እስከ ጠዋቱ 8:00 ድረስ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
