ኮሪያ ሪፐብሊክ አሸባሪው የሁቲ ቡድን በመንግሥቱ ውስጥ በሚገኙ ሲቪል ተቋማት ላይ በቅርቡ የፈጸማቸውን ደም አፋሳሽ ጥቃቶች ተከትሎ ከሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን መቆሟን ገልጻለች፤ እነዚህ ድርጊቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙም ጠይቃለች።

የኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ «በሪያድ የሚገኘውን የንጉሥ ኻሊድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ ሲቪል ተቋማትን ዒላማ ያደረጉትን የሁቲ አማፂያን የቅርብ ጊዜ ጥቃቶች አጥብቀን እናወግዛለን» ብሏል። ሚኒስቴሩ በሲቪሎችና በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ፈጽሞ ተቀባይነት እንደሌላቸው አስገንዝቧል።

በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላምና መረጋጋት መኖሩ ከዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለትና ከኃይል ደኅንነት አንጻር ኮሪያን ጨምሮ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጠቃሚ መሆኑን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፤ ለተጎጂዎች ቤተሰቦችም ልባዊ ሐዘኑን ገልጿል።