አሻርቅ አል-አውሳት ጋዜጣ እንደዘገበው፣ ሁለት የሳዑዲ ሚኒስትሮች ሰኞ ዕለት አሸባሪው የሁቲ ቡድን በዋና ከተማዋ ሪያድ ላይ የፈጸማቸውን ጥቃቶች አውግዘዋል። የሚዲያ ሚኒስትሩ ሁለቱን ቅዱስ መስጊዶች ዒላማ ማድረግ የሽብር ባሕሪ ነው ያሉ ሲሆን፣ የዕለት ተዕለት ኑሮ በመደበኛ ሁኔታ እየቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች ሁቲዎች «ለዓለም አቀፍ ሕጎችና ለሥነ ምግባር መርሆዎች ምንም ዋጋ አይሰጡም» ማለታቸውን ጋዜጣው አስፍሯል።