በዘንድሮው የሐጅ ወቅት ሳዑዳውያን ሴቶች በመካ በሚገኘው ታላቁ መስጊድ ሐጃጆችን በማገልገል ንቁና ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወቱ ሲሆን፣ ከፍተኛ ሙያዊ ብቃትና ክህሎት እያሳዩ ነው።

ሴቶችን ለማብቃት በተዘረጉ የመንግሥት ፕሮግራሞች ድጋፍ፣ የሕዝብ እንቅስቃሴን ማስተዳደር፣ ሴት ጎብኚዎችንና ሐጃጆችን በመስክ መምራት፣ የጤና አገልግሎቶችንና የሰብዓዊ በጎ ፈቃድ ሥራዎችን የመሳሰሉ ቁልፍ ተግባራትን ያከናውናሉ።

በመስክ ላይ ያላቸው ሰፊ ተሳትፎ ሳዑዳውያን ሴት ባለሙያዎች የደረሱበትን የሥልጠናና የብቃት ደረጃ ያሳያል። ይህም ሐጃጆች በምቾት፣ በእርጋታና በደኅንነት ሥርዓታቸውን እንዲፈጽሙ የሚያስችለው የተቀናጀ የአገልግሎት ሥርዓት አካል ነው።

ከኢትዮጵያ የሚመጡትን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ ሴት ሐጃጆች ከእነዚህ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ።