ሱዳን በቅድስቲቱ መዲና ከተማ ለነቢዩ መስጊድ (አል-መስጂድ አን-ነበዊ) ኤሌክትሪክ የሚያቀርበው የ‹ጠይባ› የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ኢላማ መደረጉን አጥብቃ አውግዛለች። የሳዑዲ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው፣ ሱዳን ለጥቃቱ ተጠያቂ ያደረገችው ‹አሸባሪው የሁቲ ሚሊሻ› ብላ የጠራችውን ቡድን ነው።
የሱዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ጥቃቱ የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ከተማን ክብር የሚነካና ሲቪል ተቋምን ያነጣጠረ አሳፋሪ ድርጊት መሆኑን ገልጿል።
ሚኒስቴሩ እንዳለው፣ ድርጊቱ ሁቲዎች ኢስላማዊ ቅዱሳን ስፍራዎችን ኢላማ የማድረግና በዓለም ዙሪያ ያሉ ሙስሊሞችን ስሜት የመቀስቀስ አካሄድ አካል ነው።
ሱዳን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲህ ያሉ ድርጊቶችን እንዲያወግዝና እንዲገታ ጥሪ አቅርባለች፤ ይህም የሁለቱን ቅዱሳን መስጊዶች ደኅንነትና ጥበቃ ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ገልጻለች።
በመዲና ለሚኖሩና ከተማዋን ለሚጎበኙ የማኅበረሰባችን አባላት የከተማዋ መሠረታዊ አገልግሎቶች ደኅንነት በቀጥታ የሚመለከታቸው ነው።
