የሳዑዲ ዓረቢያ ብሔራዊ የሜትሮሎጂ ማዕከል ዛሬ ባወጣው ማስጠንቀቂያ በአል-ባሃ ክልል በጣም ኃይለኛ ነፋስ የታጀበ መካከለኛ ዝናብ እንደሚጥል ገልጿል። ጎርፍ፣ የበረዶ ዝናብና ነጎድጓድ ሊከሰቱ እንደሚችሉና የአግድም እይታ ወደ ዜሮ ሊቀርብ እንደሚችልም አመልክቷል።

ማስጠንቀቂያው የአል-ባሃ ከተማን እንዲሁም የበልጁርሺ፣ የአል-መንደቅ፣ የበኒ ሐሰን፣ የአል-ቁራ፣ የአል-መኽዋ፣ የቂልዋ፣ የጋሚድ አል-ዚናድና የአል-ሐጅራ አውራጃዎችንና አጎራባች አካባቢዎችን ያካትታል። ሁኔታው በፈጣሪ ፈቃድ እስከ ምሽት 8 ሰዓት ይቀጥላል።

ማዕከሉ በሌላ ማስጠንቀቂያ በአል-አቂቅ አውራጃና አጎራባች አካባቢዎች ከነጎድጓድና ከኃይለኛ ነፋስ ጋር ቀላል ዝናብ እንደሚጥልና እይታ እንደሚቀንስ ገልጿል፤ ይህም እስከ ምሽት 8 ሰዓት ይቆያል።